Logo
Askuala S2

የአስኳላ ተዋናይ ፌስቡክ ላይቭ ቻት እንዳያመልጥዎ! - አስኳላ

ዜና
29 ሴፕቴምበር 2021
ፌስቡክ ላይቭ ከአስኳላ ተዋናይ ጋር።

በተወዳጁ አስኳላ በተሰኘው አስቂኝ ድራማ ላይ የሚተውኑት ደመወዝ ጎሽሜ፣ ማማሩ ተስፋ እና ዘላለም ምፅላልን በአቦል ቲቪ ዋና በፌስቡክ ፔጅ ላይ በላይቭ ቻት ያግኟቸው!

ደመወዝ ጎሽሜ አስቂኙ የኔታ የተሰኘውን ገጸ-ባህሪ ሆኖ በአስኳላ ድራማ ላይ ይተውናል። የኔታ አስኳላ የተባለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመዝግበው የሚያጋጥማቸውን አስቂኝ ጊዜያት በድራማው ላይ እንመለከታለን።

ለአስኳላ እና የየኔታ ገጸ፡ባሀሪ ዙሪያ ያለዎትን ጥያቄ ለተዋናይ ደመወዝ ጎሽሜ መስከረም 21 አርብ ከምሽቱ 1:00 በአቦል ቲቪ ፌስብክ ላይቭ ቻት ላይ ማቅረብ ይችላሉ!

1632919653 28 askual

የእንቅስቃሴ ሳይንስ ትምህርትን ከአኗኗር ጋር አገናኝቶ የሚያስተምረው ማእበል የተሰኘው ገጸ-ባህሪን ሆኖ የሚተውነው ዘላለም ምፅላል መስከረም 28 አርብ ከምሽቱ 1:00 በአቦል ቲቪ ፌስቡክ ላይቭ ቻት ላይ ይቀርባል!

1632919762 28 askualal 2

በመጨረሻም ተወዳጁ ይነበብ የተባለውን ገጸ-ባህሪ ሆኖ የሚተውነው ማማሩ ተስፋ ጥቅምት 5 አርብ ከምሽቱ 1:00 በአቦል ቲቪ ፌስቡክ ላይቭ ቻት ጥያቄዎን ለመመለስ እና አስተያየትዎን ለመቀበል ይቀርባል!

1632920039 28 screenshot 2021 09 29 at 14.53.18

የአስኳላ ተዋናይ ፌስቡክ ላይቭ ቻት በአቦል ቲቪ ዋና ፔጅ ላይ እንዳያመልጥዎ!

አስኳላ ድራማ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ ይከታተሉ!