channel logo
Ashara S1

የአላዛር ቤተሰብ ከእሱ ምንድን ነው የሚፈልጉት?

ዜና
23 ዲሴምበር 2024
አላዛር በህይወት በመገኘቱ የሁለቱም ቤተሰቡ ህይወት ተቀይሯል ነገር ግን ቤተሰቦቹ ምንድን ነው የሚፈልጉት?
ashara article - what does the family want?

አላዛር ለአመታት በመጀመሪያ ቤተሰቡ ሲፈለግ ሁለተኛ ቤተሰብ መስርቶ ደስተኛ ኑሮ እየኖረ ነበር። ይህ አላዛር ማንነቱን ካለማስታወሱ የተፈጠረ አለመግባባት ነው። አሁን ግን አላዛር አለመሞቱ ታውቋል እናም የሁለት ቤተሰቡን ፍላጎት ለመፈጸም የሚያደርገው ጥረት ሊያስደስታቸው አልቻለም።

ስለዚህ ጥያቄው ይሄ ነው ቤተሰቡ ከእሱ ምንድን ነው የሚፈልጉት?

  1. ትዝታ እና ማርቆስ

ማርቆስ የአላዛር ቤተሰብ አይደለም በተቀራኒው አላዛር ማንነቱን የመርሳቱ ምክንያት እሱ እና ትዝታ ናቸው። ስለዚህ ፍላጎታቸው አንድ ነው። ትዝታ የአላዛር በህይወት መኖር ከማርቆስ ጋር ምን አንዳደረገችው የማስታወስ እድሉ ይተልቃል ማለት ነው ብላ ታምናለች ስለዚህ የአላዛርን ድርጊት መከታተል ትፈልጋለች። ነገር ግን አላዛር ሌላ ቤተሰብ እንዳለው ስታውቅ የቅናት ስሜት አንደተሰማት ያስታውቃል። አላዛር ትዝታ እና ማርቆስ የሚፈልጉትን ማድረግ አይችልም።

  1. ምስራቅ እና ጋሽ ናንጌ

ጋሽ ናንጌ አላዛርን አንደ ልጃቸው ስለሚያዩት በመዋሸታቸው በጣም ተቆጭተዋል። ነገር ግን አላዛር ቤተሰባቸውን ትቶ አዲስ አበባ በመሄዱ ተከፍተዋል ምክንያቱም ልጃቸው ምስራቅን በጣም ጎድቷታል። ምስራቅ አላዛር ትቷት በመሄዱ ምክንያት እራሷን ለማጥፋት ወደ መሞከር ደርሳለች። ምስራቅ ከአላዛር የምትፈልገውን በግልጽ ተናግራለች፣ አላዛር እሷን እና ልጆቿን ትቶ እንዳይሄድ እና እንዳይረሳቸው ነው። ነገር ግን እውነቱን በመደበቋ ይሄን ማግኘት አልቻለችም፣ አሁን አላዛር ጋር አዲስ አበባ በመሄዷ ፍላጎቷ ይሟላ ይሆን ወይስ አይበቃትም? በእዚህ ሁሉ ማሃል ደግሞ ከልጇ አባብል ይልቅ የራሷ ፍላጎት አስበልጣለች፣ አባብል ይቅር ይላት ይሆን?

  1. ዮናስ

ዮናስ አንድ ወንድሙን አላዛርን በህይወት በማግኘቱ ብቻ ደስተኛ ነው። ነገር ግን በዙሪያው ያሉት ሰዎች የእሱ አይነት ደስታ እንዳልነበራቸው ሲያውቅ የወንድሙን ማስታወስ አለመቻል መንስ ለማወቅ ይፈልጋል። በተጨማሪም የአላዛር እና ቤተሰቡን ግንኙነት ለማስተካከል ይሞክራል ነገር ግን ቤርሳቤህ አባቷን ለምን መቀበል እንዳልፈለገች ሊያውቅ አልቻለም።

  1. ቤርሳቤህ

የአላዛር መገኘት ከማንም በላይ ነው የቤርሳቤህን ህይወት የረበሸው። ቤርሳቤህ ገና በልጅነቷ አባቷን አጥታ ከብዙ አመታት በኋላ በህወት አለ እናም ሌላ ቤተሰብ መስርቶ እየኖረ ነበር ስትባል ያልተጠበቀ መልስ ስላላት መወቀስ አትችልም። ነገር ግን ምንም ያህል አባቷን መቅረብ ብትፈልግም እራሷን እየከለከለች ነው። የቤርሳቤህን ፍላጎት ማወቅ አይቻልም ግን ከአባቷ ጋር እንደሚገናኝ እርግጠኛ ነን።

የአሻራ ገጸ ባህሪያት የሚፈልጉትን ነገር ከአላዛር የሚያገኙ ከሆነ ለማወቅ፣ ድራማውን ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት።