channel logo
Ashara S1
channel logo

Ashara

465TelenovelaPG13

የአሻራ ድራማ የመጀመሪያ እይታ

ዜና
30 ኦገስት 2024
አዲሱ የአቦል ቲቪ ድራማ የተጀመረው በባልና ሚስት መካከል ያለው ፍቅር ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ፣ አንድ ውሳኔ እንዴት ህይወትን እንደሚቀይር እያሳየ ነው።
ashara article 2

የመጀመሪያው የአሻራ ክፍል የአላዛርን ቤተሰብ አቅርቧል ነገር ግን ይሄንን ፍጹም የመሰለ ቤተሰብ ቀረብ ብለን ስንመለከተው የተደበቁትን ስሜቶች ተገንዝበናል። አላዛር የሚሰራበትን መስሪያ ቤት ስም የሚያስጠራ ፈጠራ በመስራቱ ሽልማት ይቀበላል። ለዚህ ደስታውን አጣጥሞ ሳይጨረስ የድሮ ሰራተኛ በስካር እራሱን እንዲከላከል ሲያስጠነቅቀው የተደበቀ ነገር እንዳለ መጠርጠር ይጀምራል።

በሌላ በኩል ደግሞ ሚስቱ ትዝታ አላዛር ስለረዱት ካመሰገናቸው ሰዎች አንዷ ባለመሆኗ ስሜቷ ይጎዳል። ግን በቀጣይ በማህላቸው የሚፈጠረው ነገር በዝህ ምክንያት ይሆን?

አላዛር በስራ ቦታው የተደበቀውን ነገር ሰምቶ በድንጋጤ ወደ ቤት ሲመለስ ሚስቱን ከድሮ ፍቅረኛዋ ማርቆስ ጋር ያገኛታል። በንዴት ከሁለቱ ጋር ሲጣላ ማርቆስ በሻማ ማስቀመጫ መትቶት እራሱን ይስታል። ይህ አንድ ድንገተኛ ሁኔታ ግን የሶስቱንም ሰዎች ህይወት መስመር ይቀይራል።

አላዛር ሞቷል ብለው ያመኑት ትዝታ እና ማርቆስ ጫካ ወስደው ይጥሉታል ነገር ግን በመሃላቸው ያለውን ትልቅ ወንጀል መቋቋም ባለመቻላቸው ጸብ ውስጥ ይገባሉ። ሞቷል ተብሎ የታመነው አላዛር ደግሞ ጫካው አካባቢ የሚኖሩት እና በሽፍታው ልጃቸው ምክንያት ነው የተጎዳው ብለው የሚያምኑት አቶ ናንጌ ያተርፉታል።

መትረፉን ያላወቁት ትዝታ እና ማርቆስ ወንጀላቸውን ለመደበቅ እቅድ ያደርጋሉ  አሁን አላዛር ነቅቷል። አላዛር የደረሰበትን ጉዳት ተቋቁሞ ወደ ቤቱ መመለስ ይችል ይሆን? እርስዎ ምን ያስባሉ?

Ashara S1
Ashara S1 Poll 3

አላዛር እውነቱን ማጋለጥ ይችላል?

Click here to make your selection
አይችልም
ይችላል

#አሻራ ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2:00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት።