channel logo
Ashara S1
channel logo

Ashara

465TelenovelaPG13

አሻራን የምንመለከትበት 3 ምክንያቶች

ዜና
12 ኦገስት 2024
ከአሻራ ድራማ የምንጠብቃቸው አጓጊ ነገሮች እነዚህ ናቸው።
Ashara S1

አሻራ ድራማ አዲሱ የአቦል ቲቪ ቴሌኖቬላ ነው። በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ሰኞ ነሀሴ 6 ከምሽቱ 2፡00 ይጀምራል። ድራማው የሚያጠነጥነው በአላዛር ህይወት ታሪክ ሲሆን አላዛር የብዙ ጊዜ ልፉቱን የፈጠራ ውጤት በክብር አግኝቶ ብሩህ ተስፋ ከፊቱ የሚጠብቀው ቢመስልም በድንገት ህይወት ባላሠበው መሥመር ትወስደዋለች። እኛ የአላዛርን ታሪክ በአሻራ እንድንከታተል ያደረጉን 3 ምክንያቶች እነዚህ ናቸው

  1. በዝነኛ ኮከቦች የተሞላ አቅርቦት ነው።

በቅርብ ቀን በማህበራዊ ሚዲያ በተለቀቀው የተዋናይ ማንነት ከሆነ ከድራማው በጣም ምርጥ ብቃት መጠበቅ እንደምንችል ያረጋግጥልናል! ከዚህ በፊት በአቦል ታይተው የማይታወቁት ተዋናይ ዘቢብ ሀይሉ እና ብሩክታዊት ሳሙኤልን በጉጉት እንጠብቃለን። ኤሊያስ ወሰንየለህ እና መሳይ ግርማ ደግሞ ከዚህ በፊት በደራሽ እና ሁለት ጉልቻ ተደምመንባቸው ነበር ስለዚህ ድራማውን በጉጉት እንድንጠብቅ አድርጎናል።

  1. ለየት ያለ አዲስ ይዘቱ።

በድራማው አጭር ቅምሻ እንዳየነው ከሆነ የአላዛር ህይወት በአንድ ውሳኔ ምክንያት ነው አቅጣጫው የቀየረው። ስለዚህ አላዛር እንዴት እዛ ቦታ ላይ ደረሰ? አንድ ሰው የሁለት ቤተሰብ አባወራ እንዴት ሊሆን ቻለ? ድራማው ላይ መልሱን እስከምናገኝ በጉጉት እየተጠባበቅን ነው!

  1. በሳምንት 3 ቀን መመልከት ስለምንችል።

አሻራ ድራማ ሳምንታችንን በልብ አንጠልጣይ ታሪኩ ያደምቀዋል። ይህ ማለት ከስራ ወይም ትምህርት በኋላ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት መጠበቅ የምንችለው አስተማማኝ መዝናኛችን ነው ማለት ነው። በጣም ጓግተናል!

Ashara S1
Ashara S1 Poll 1

አሻራን ለመመልከት በምን ያህል ጉጉት እየተጠባበቁ ነው?

100% 😍11%
1000000000000% 🔥89%

#አሻራ ሰኞ ነሀሴ 6 ከምሽቱ 2፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል!