አደይ የአቦል ቲቪ ተወዳጅ ድራማ ከ አንዲት 17 አመት ልጃገረድ ጋር የተሳሰረውን የሁለት ቤተሰብ ህይወት እና ጉዞን የሚከታተል ድራማ ነበር።
ተዋናይት በእምነት ሙሉጌታ የተወዳጇ አደይን ገጸ ባህሪ ስሜት በሚነካ መንገድ በመተወን የብዙ ተከታታዮችን ልብ ሰርቃለች። አደይ ድራማ በአቦል ቲቪ በ6 ምዕራፎች ተመልካቾችን በፍቅር፣ ጥበብ፣ ሳቅ እና ጨዋታ ሲያዝናና ቆይቷል። የመጨረሻው ክፍል መጋቢት 21 2015 በአቦል ቲቪ ቀርቦ ነበር።
የአደይ መጨረሻ ክፍል ካመለጥዎ ይሄን ይመልከቱ።
የአደይን ፍፃሜ በማስመልክት ለተወዳጁ የአደይ ተዋናይ ቸርነት ነጋሽ አንድአንድ ጥያቄዎች አቅርበናል።
ተዋናይ ቸርነት ነጋሽ እባላለሁ። በቅድሚያ ዲኤስቲቪ አና አቦል ቲቪን ላመሰግን እወዳለው። ወደ ጥያቄዎቹ ስገባ፦
- በአደይ ላይ የነበረዎትን የስራ ጊዜ ምን ይመስል ነበር?
በድራማው ቆይታዬ ከሁሉም ተዋናይና ክሩ ጋር ፍፁም ቤተሰባዊ በሚመሰል መልኩ ሳሳልፍ አንደነበረ ነው የተሰማኝ። ከፕሮዳክሸኑም ጋር ጥሩ በሚባል የስራ ግኑኝነት ስለ ነበረኝ እስከመጨረሻው ክፍል ድረስ አብሬአቸው ተጉዣለው።
- ከተወኑት ገጸ ባህሪ [አቶ ግርማ] ምን ተምርያለሁ ማለት ይችላሉ?
አንደ ቤተሰብ የማየት ስሜት ተጋብቶብኛል ከሰው ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል ተምሬአለሁ።
- በመጨረሻ፣ ለተመልካቾች ምን መልዕክት አልዎት?
ሳትሰለቹን ለሰጣችሁን ክብርና አድናቆት ማመሰገን አፈልጋለው።
ለአደይ ፍጻሜ ዝግጁ ካልሆኑ አቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 በመከታተል አደይን ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 መመልከት ይችላሉ!