Logo
Adey S6

የአደይ ገጸ ባህሪያት የድሮ እና የአሁን ማንነቶች

ዜና
31 ሜይ 2024
የአደይ መንገድ በውጣ ውረድ የተሞላ ነበር ግን አሁን መጨረሻው ደርሷል።
adey s6 article

የአደይ ታሪክ የጀመረው አዲሱ የዲኤስቲቪ ቻናል አቦል ዱካ ሲጀመር ነው። የዋና ገጸ-ባህሪያችን የአደይ ታሪክ የሚጀምረው ትንሹ ኩርኩሪት ከተማ ሲሆን፣ የፋሽን ዲዛይነር ለመሆን እና የቤተሰቧን ሕይወት ለመለወጥ የመማር ሕልም ነበራት። አደይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ቀናተኛ ሴት ነበረች። ቤቷን ለቃ እንድትሄድ ፣ በሞግዚትነት እንድትሰራ እና የመጀመሪያ ፍቅሯን በአንድ ጊዜ እንድታገኝ የሚያደርጓትን ክስተቶች አልጠበቀቻቸውም ነበር።

አሁን የምናውቃት አደይ ደግሞ በጣም ጠንካራ የሆነ ሰው እንኳ እንዲሸነፍ የሚያደርጉ ተግዳሮቶች አጋጥሟታል። አሁን የምናውቃት አደይ አፍቅራለች፣ አጥታለች፣ የቤተሰቧ እና የእሷ ስም በመጥፎ ተነስቷል፣ በሙያዋ አድጋለች፣ ትልቅ ኩባንያም ትመራለች። የሚገርም እድገት አይተንባታል።

Adey S6 Poll BG 3
adey s6 poll 1

እርስዎ የትኛዋን አደይ ይበልጥ ይወዷታል?

የድሮዋን አደይ6%
የአሁኗን አደይ94%

አቤል ሁሉም ነገር ያለው ሀብታም ልጅ፣ ቀለል ባላ የስራ ምክንያት የተፈጠረው ክስተት የሕይወቱን አቅጣጫ ቀይሮታል። ከዚህ በፊት የምናውቀው አቤል ትዕቢተኛ ነበር እናም ሥራውን ሳያከናውን ሁሉንም ነገር ማግኘት ይችላል ብሎ ያምን ነበር። እሱ በቀላሉ የሚታለል እና በዙሪያው ያሉትን ሰዎች በቀላሉ ያምን ነበር።

በሌላ በኩል አሁን የምናውቀው አቤል ብቃት ያለው ሠራተኛ ነው እናም ያለውን ሁሉ ለማግኘት ጠንክሮ ሰርቷል፣ በፍቅር ስህተቶችን ሰርቷል ፍቅሩን ሊያጣ ጫፍ ደርሶ ነበር ነገር ግን በመጨረሻው ሰከንድ እራሱን በማስተካከል አደይን አግብቷል። አሁን የምናውቀው አቤል ህልሙን አሳክቷል።

Adey S6
adey s6 poll 2

እርስዎ አቤል ስለፍቅር በቂ ትምህርት ተምሯል ብለው ያምናሉ?

አዎ ተምሯል83%
አይ አልተማረም17%

ለፍቅር ሁሉንም ነገር አደጋ ላይ የጣለው እና በሌሎች ላይ መተማመንን መማር ያስፈለገው ምስጢራዊው ሁንአንተ የማይረሳ ለውጥ አድርጓል። እሱ በፍቅር ሲወድቅ ሁሉም ጠቅልሎ ነበር የሚገባው ይህም አስከፊ መዘዞችን ያስከተሉ አስደንጋጭ ባህሪያትን አስከትሏል።

አሁን የምናውቀው ሁንአንተ ባለትዳርና አባት ነው። ለመበቀል ሲል የሞተ ካስመሰለው ሰው እና ሰው ከሚያግተው ሰው እሩቅ ነው። ሁንአንተ የፍቅርን ትርጉም ተገንዝቦ በዙሪያው ላሉት ሰዎች እንዴት የተሻለ ሰው መሆን እንደሚቻል ተምሯል።

Adey S6
adey s6 poll 3

እርስዎ ሁንአንተን ይደግፉት ነበር?

አዎ እደግፋለሁ100%
አይ አልደግፍም0%

ዋናው ገጸ-ባህሪዎቻችን አሁን የሆኑትን ሰዎች እንዲሆኑ ከፍተኛ ለውጦችን እና ብዙ ተግዳሮቶችን አልፈዋል። ይሄንንም መመልከት በጣም አስደሳች ጊዜ ነበር።

Adey S6
adey s6 poll 4

እርስዎ የማንን እድገት በጣም ወደውታል?

አደይ 20%
አቤል 20%
ሁንአንተ60%

የመጨረሻው የ #አደይ ክፍል ዛሬ ከምሽቱ 2፡00 በ #አቦልዱካ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 እንዳያመልጥዎ!